ማባዛት ማለት ከመደመር፣ መቀነስ፣ ማካፈል ጋር እንደ አራቱ መሰረታዊ የቁጥር ሂሳብ ስሌቶች የሚታይ ነው። ስራውም አንድን ቁጥር በሌላ ቁጥር ማብዛት ነው።
የማባዛት ምልክት.
ማባዛት: የጥንቱ የኢትዮጵያውያን ዘዴ
በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰራበት የነበረው የማባዛት ዘዴ በምሳሌ እንሆ።
12ን በ13 ለማባዛተ ከፈለግን እንዲህ እናረጋለን፡-
12*13
አንደኛውን ቁጥር በ2 ካበዙ በኋላ ሌላኛውን ደግሞ በ2 ያካፍላሉ፣ ተካፍሎ የቀረውን ይተውታል
በሁለት ማብዛት..... በሁለት ማካፈል
12 ................13
24 .................6
48 .................3
96 .................1
|
ከዚያ በቀኝ በኩል በሚገኙት የማይካፈሉ (odd) ቁጥሮች ትይዩ ያሉትን የግራ ቁጥሮች ይደምራሉ። በምሳሌያችን ላይ እንደሚታየው 13፣ 3 እና 1 በቀኝ የማይካፈሉ ቁጥሮች ሲሆኑ፣ በነሱ ትይዩ ያሉትን ስንደምር
12+48+96= 156
ይህ ዘዴ ለኮምፒውተር ስራ አገልግሎት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይቻላል ምክንያቱም ከባይናሪ የቁጥር ስርዓት ጋር ተዛማጅነት ስላለው።