መጋቢት ፳፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፹፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፩ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፳፻፲ ዓ.ም. - ዶ/ር ዓቢይ ኣሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
ልደት
- ፲፱፻፵ ዓ.ም - የእንስሳት ሕክምና ባለሙያውና የግዕዝ ፊደላትን በኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ያደረጉት ምሁር ዶ/ር ኣበራ ሞላ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ አቡነ ዮሐንስ-ጳውሎስ በ፹፬ ዓመት ዕድሜያቸው አለፉ።
ዋቢ ምንጮች