የኦሮሞ ቀበሌኞች በኢትዮጵያና በኬንያ የሚያሳይ ካርታ
ኦሮምኛ ወይም አፋን ኦሮሞ(Afaan oromoo ,
) በአፍሪካ ደረጃ ከአረብኛ እና ሃውዛኛ ቀጥሎ በብዛት የሚነገር ቋንቋ ነው። 263,000 የሚደርሱ ተናጋሪዎች በጎረቤት ሃገሮች ሶማሊያ እና ኬኒያ እንዳሉ ታውቋል። በአጠቃላይ ከ25 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች በኢትዮጵያ እና በኬኒያ ይገኛሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቋንቋውን ለመጻፍ የሚጠቀመው የላቲን ፊደል ነው። ኬንያ ውስጥ የኣሉት ኦሮሞዎች ኦርማ በሚባል የነገድ ስም ይታወቃሉ።